ወጣቶች ለመጤ አሉታዊ ልማዶችና ሱሰኝነት ተጋላጭ ከሚያደርጉ ነገሮች መራቅ እንዳለባቸው ተገለፀ

You are currently viewing ወጣቶች ለመጤ አሉታዊ ልማዶችና ሱሰኝነት ተጋላጭ ከሚያደርጉ ነገሮች መራቅ እንዳለባቸው ተገለፀ

AMN – ጥር 20/2018 ዓ.ም

ወጣቶች ለመጤ አሉታዊ ልማዶች እና ሱሰኝነት ተጋላጭ ከሚያደርጉ ነገሮች መራቅ እንዳለባቸው ተገለፀ ።

የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ወጣቶችን ታሳቢ ያደረገ አሉታዊ ልማዳዊ ድርጊቶችን፣አደንዛዥ ዕፅ እና ሱሰኝነትን ለመከላከል የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሂዷል።

የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ክብረዓለም ደምሴ፣ ሱሰኝነት አምራች ዜጋን በማሣጣት በሀገር የኢኮኖሚ ዕድገት ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ጫናን የሚያሳድር መሆኑን ጠቁመዋል።

ወጣቶች ለመጤ አሉታዊ ልማዶችና ሱሰኝነት ተጋላጭ ከሚያደርጉ ነገሮች መራቅ እንደሚገባቸው ጠቁመው፣ ቢሮው ወጣቶች ራሳቸውን የሚያንፁበት የወጣት ስብዕና ግንባታ ማዕከላትን በማጠናከር የስፖርት ማዘውተርያ ስፍራዎችንም በማስፋት በትኩረት እየሠራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ወጣቶች ራሳቸውን አለፍ ሲልም ሀገርን ከሚጎዳ አላስፈላጊ ልምምድ መቆጠብ እንዳለባቸው የተናገሩት ደግሞ የመድረኩ ተሳታፊዎች ናቸው።

እንደነዚህ ዓይነት የወጣቱን አመለካከት የሚቀይሩ የግንዛቤ መፍጠሪያ መድረኮች መጠናከር እንዳለባቸውም አስተያየታቸውን ሠጥተዋል።

በመድረኩ ከሁሉም ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ ወጣቶች፤የሥራ ሀላፊዎች እና ተጋባዥ እንግዶች ተሳትፈዋል።

በፀጋ ታደለ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review