AMN- ጥር 21/2018 ዓ.ም
የገቢዎቸ ሚኒስቴር በበጀት አመቱ ስድስት ወራት 709 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡን ገለፀ፡፡
የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን የ2018 የ6 ወራት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ በቢሾፍቱ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡
በበጀት አመቱ ስድስት ወራት 640 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 709 ቢሊዮን ብር መሰብሰብ መቻሉን የገቢዎች ሚኒስትር ዓይናለም ንጉሴ ገለፀዋል::
ሚኒስትሯ በኢትዮጵያ የተተገበረው የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎረም ውጤታማነት አንዱ መለኪያ የሃገር ውስጥ ገቢ አቅምን በማሻሻል የበጀት ጉድለትን ማጥበብ እንዲሁም የማይበገር ኢኮኖሚ መገንባት ነው ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ በፍጹም ወደኋላ የማይቀለበስና መቀጠል ያለበት ለውጥ ላይ እንደሆነች የገለፁት ሚኒስትሯ የለውጡ አካል መሆን እና ለዚሁ ለውጥ እውን መሆን ኃላፊነታችንን መዘንጋት የለብንም ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል::
በመድረኩ ህግና ስርዓትን ተከትለው ቀረጥና ታክሳቸውን በተገቢው መጠንና ጊዜ ለሚከፍሉ ግብር ከፋዮች ምስጋና መቅረቡን ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡