AMN- ጥር 24/2018 ዓ.ም
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በባህር ዳር ከተማ የሚገኘውን አማጋ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካን መጎብኘታቸውን ገልጸዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ በቅርቡ ወደ ስራ የገባው ፋብሪካው ተከላው ሙሉ በሙሉ በቅርብ ሲጠናቀቅም በዋናነት ብርድ ልብስ፣ የአልጋ ልብስ፣ የሶፋ ልብስ፣ መጋረጃ፣ የአንሶላ ጨርቅ፣ ጂንስ እና ሁሉንም አይነት የጨርቃ ጨርቅ ምርቶች በተለየዩ ዲዛይኖች እና ልኬት ማምረት ያስችለዋል ብለዋል።
ጥራት ያላቸው ተኪ ምርቶችን የሚያመርቱ እና በቀጥታ ምርቶችን ለውጭ ገበያ ከማቅረብ ይልቅ የሀገር ውስጥ ገበያውን ለማረጋጋት የሚጥሩ ፋብሪካዎች ሀገራዊ አበርክቷቸው ቀላል የሚባል እንዳይደለም አስገንዝበዋል።