AMN – ጥር 29 /2018 ዓ.ም
በዓይነቱ የመጀመሪያ እና ልዩ የሆነው የገላን ትራውማ ሆስፒታል ግንባታው መጠናቀቁንና የሕክምና መሳሪያዎች እየተሟሉለት እንደሚገኝ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡
ከንቲባዋ ይህን የገለጹት ፣ የከተማ አስተዳደሩን የስድስት ወራት ሥራ አፈጻጸም ለከተማዋ ምክር ቤት ሲያቀርቡ ነው፡፡
ከንቲባዋ በሪፖርታቸው ፣ አዲስ አበባን የጤና ቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ የሚያስችሉ ሶስት አዳዲስ ሆስፒታሎች ግንባታ መከናወናቸውንም ጠቅሰዋል፡፡

የኮልፌ መንዲዳ እና የንፋስ ስልክ ላፍቶ ሁለት ግዙፍ ዘመናዊ ሆስፒታሎች ከ500 አልጋ በላይ የሚይዙ መሆናቸውንም ጠቅሰዋል ፡፡
በሀገራችን በዓይነቱ የመጀመሪያ እና ልዩ የሆነው የገላን ትራውማ ሆስፒታል ከ511 በላይ አልጋዎች እንደሚኖሩት ከንቲባዋ ገልፀዋል ፡፡
ሶስቱ አዳዲስ ሆስፒታሎች ግንባታቸው መጠናቀቁንና የሕክምና መሳሪያዎች እየተሟሟላቸው እንደሚገኙ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል፡፡
በታደሰ ሽፈራው