AMN – ጥር 29/2018 ዓ.ም.
የጤና ተቋማትን ፍትሐዊ ተደራሽነት ለማሳደግ 9 አዲስ ጤና ጣቢያዎች ተመርቀው ወደሥራ መግባታቸውን የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል።
ከንቲባ አዳነች የከተማ አስተዳደሩን የስድስት ወራት ሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ለከተማዋ ምክር ቤት ባቀረቡበት ወቅት እንደተናገሩት አዲስ ከተገነቡት ጤና ጣቢያዎች በተጨማሪ 13 ጤና ጣቢያዎች ሰፊ የማስፋፊያ ግንባታ እንደተከናወነላቸው ይገኛል።

በዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል ነባሩን የሆስፒታል አቅም ከእጥፍ በላይ የሚያሳድግ የላቀ ሕክምና ማዕከል መገንባቱን እና በዘመናዊ የሕክምና መሳሪያዎች እንዲደራጅ መደረጉን ነው ከንቲባዋ የገለጹት።
የራስ ደስታ ዳምጠው መታሰቢያ ሆስፒታል እና የዳግማዊ ምኒሊክ ሪፈራል ሆስፒታል ግዙፍ የማስፋፊያ ግንባታ ተደርጎላቸው በዘመናዊ ሕክምና ግብዓቶች እየተሟሉላቸው መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
ከንቲባዋ ባቀረቡት ሪፖርት ሁሉም ሆስፒታሎች የራሳቸው የኦክስጅን ማምረቻና ዘመናዊ የኦክስጅን አገልግሎት መስጫ አሠራር እንዲኖራቸው ተደርጓል ብለዋል፡፡
በታደሰ ሽፈራው