AMN – ጥር 29/2018 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባዔውን እያካሄደ ይገኛል፡፡ በጉባዔው ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የከተማ አስተዳደሩን የ6 ወራት የሥራ አፈፃጸም ሪፖርት አቅርበዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት 6 ወራት ለ178 ሺህ 500 ነዋሪዎች ቋሚ የሥራ ዕድል ለመፍጠር አቅዶ ወደ ሥራ የገባ ቢሆንም፣ በተደረገው ከፍተኛ ጥረት ለ195 ሺህ 112 ዜጎች ቋሚ የሥራ ዕድል በመፍጠር ከዕቅድ በላይ ማሳካት መቻሉን ከንቲባዋ ገልጸዋል።

የከተማ አስተዳደሩ በተያዘው የሥራ ዘመን ለዜጎች ዘለቄታዊ የሥራ ዕድል በመፍጠር እና ድህነትን በመቀነስ ረገድ ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገቡን ከንቲባዋ በሪፖርታቸው ገልጸዋል።
በከተማዋ በተከናወኑ የተቀናጁ ሥራዎች የሥራ ዕድል ፈጠራ ግቡን 109 በመቶ ማሳካት የተቻለበት መሆኑን ከንቲባዋ ተናግረዋል።
በታምራት ቢሻው