የህዝብ ሀብት በሆነ ትራንስፎርመር ላይ የተቃጣ ዘረፋ በፀጥታ ኃይሎች ከፍተኛ ክትትልና ጥረት ከሸፈ

You are currently viewing የህዝብ ሀብት በሆነ ትራንስፎርመር ላይ የተቃጣ ዘረፋ በፀጥታ ኃይሎች ከፍተኛ ክትትልና ጥረት ከሸፈ
  • Post category:ሙስና

AMN ጥር 30/2018 ዓ.ም

በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ አስተዳደር ለህዝብ አገልግሎት እየተዘረጋ ያለ ትራንስፎርመር ዘርፈዉ ለመሰወር ያደረጉት ሙከራ በፀጥታ ኃይሎች ትልቅ ክትትልና ጥረት በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለፀ።

ድርጊቱ የተፈፀመዉ በክ/ከተማዉ ወረዳ 13 ልዩ ቦታዉ ሀይዌይ አካባቢ ከለሊቱ 8 ሰዓት አካባቢ ነዉ፡፡

ዘራፊዎች በተደራጀ ሁኔታ መኪና በመያዝ አዲስ እየተዘረጋ ያለ ትራንስፎርመር ሰርቀዉ ለመሰወር ሲሞክሩ በፀጥታ አካላት ከፍተኛ ጥረት ዘራፊዎቹ ለድርጊቱ የተጠቀሙበትን ተሽከርካሪ በቁጥጥር ስር በማዋል ትራንስፎርመሩን ማዳን ተችሏል፡፡

ፖሊስ ስርቆት የፈፀሙ ግለሰቦችን በህግ ጥላ ስር ለማዋል ክትትል እየተደረገ ይገኛል።

ለመሰረተ ልማት የተዘረጉ የህዝብ መገልገያ ንብረቶችን የሚዘርፉ እና ጉዳት የሚያደርሱ ግለሰቦችም ሆኑ ቡድኖች ከህግ አይን ሊሰወሩ እንደማይችሉ እና የፀጥታ ኃይሉ ከህብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት ተገቢዉን ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ አሳዉቋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review