ብልጽግና ፓርቲ አዲስ የምርጫ መወዳደሪያ ምልክት እና ማኒፌስቶ ይፋ አደረገ

You are currently viewing ብልጽግና ፓርቲ አዲስ የምርጫ መወዳደሪያ ምልክት እና ማኒፌስቶ ይፋ አደረገ

AMN — የካቲት 03/ 2018 ዓ.ም

ብልጽግና ፓርቲ በ7ኛው ሀገር አቀፍ ጠቅላላ ምርጫ የሚወዳደርበትን አዲስ የምርጫ ምልክት እና ማኒፌስቶ ይፋ አድርጓል።

የምርጫ ምልክቱ “የስንዴ ነዶ” መሆኑንም ፓርቲው አስታውቋል።

የፓርቲው ምክትል ፕሬዝዳንቶች አቶ ተመስገን ጥሩነህ እና አቶ አደም ፋራህ የፓርቲያቸውን የምርጫ ምልክት እና ማኒፌስቶ ይፋ አድርገዋል።

ብልፅግና ፓርቲ “ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር” በሚል መሪ መልዕክት በምርጫ 2018 እንደሚወዳደርም አስታውቋል።

ምርጫውን ካሸነፈ በቀጣይ 5 ዓመት በ15 ዓምዶች የተዋቀረ ኢትዮጵያዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ እንደሚሰራ በማኒፌስቶው አብራርቷል።

በካሳሁን አንዱዓለም

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review