የአፍሪካ-ጣሊያን ፎረም በአዲስ አበባ መካሔዱ ኢትዮጵያ አፍሪካን ከተቀረው ዓለም ጋር ለማስተሳሰር ያላትን አቅም የሚያሳይ ነው – የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት

You are currently viewing የአፍሪካ-ጣሊያን ፎረም በአዲስ አበባ መካሔዱ ኢትዮጵያ አፍሪካን ከተቀረው ዓለም ጋር ለማስተሳሰር ያላትን አቅም የሚያሳይ ነው – የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት

AMN – የካቲት 5፣ 2018 ዓ.ም።

የአፍሪካ-ጣሊያን ፎረም በአዲስ አበባ መካሔዱ ኢትዮጵያ አፍሪካን ከተቀረው ዓለም ጋር ለማስተሳሰር ያላትን አቅም የሚያሳይ መሆኑን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ገለጸ።

የአፍሪካ-ጣሊያን ፎረም መካሔድ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ከሮም ውጪ ሲካሄድ የዘንድሮው ለመጀመሪያ ጊዜ ነው፡፡

የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት በሳምንቱ የሚካሔዱትን የአፍሪካ-ጣሊያን እና የአፍሪካ ሕብረት ጉባዔን አስመልክቶ በዛሬው ዕለት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

የአፍሪካ ጣሊያን ፎረም፣ የአፍሪካና ጣሊያን ግንኙነት በአሕጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ትብብር ዘርፎች ይበልጥ እንዲጠናከር የሚያደርግ ነው መሆኑን ገልጿል፡፡

በታደሠ ሽፈራው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review