በፀጥታው ምክር ቤት የአፍሪካ ቋሚ መቀመጫ አለማግኘት መከላከያ የሚቀርብለት ጉዳይ አይደለም-የተመድ ዋና ፀኃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ

You are currently viewing በፀጥታው ምክር ቤት የአፍሪካ ቋሚ መቀመጫ አለማግኘት መከላከያ የሚቀርብለት ጉዳይ አይደለም-የተመድ ዋና ፀኃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ

AMN-የካቲት 07/2018 ዓ.ም

አለመተማመን እና መከፋፈል በሰፈነበት ዓለም የአፍሪካ ህብረት ለባለብዙ ወገን ትበብር ምሳሌ ነው።

ለፍትህ እና እኩለነት አህጉሪቱን በተመለከተ በተለያዩ ሁኔታዎች እና ቦታዎች ድምፃቸውን ማሰማታቸውን የገለፁት ዋና ፀኃፊው ባለፈው አስርት አመት የህብረቱ እና የተባበሩት መንግስት ድርጅት ትብብር ወደ አዲስ ምዕራፍ መሻገሩንም ተናግረዋል።

ተ.መ.ድ ከአፍሪካ ህብረት ጋር በሰላምና ፀጥታ፣ በዘላቂ ልማት እና በሰብዓዊ መብት ጥበቃ ዙሪያ በቅርበት እየሰራ እንደሚገኝም ገልፀዋል።

አፍሪካ በጠረጴዛው ዙሪያ መኖር አለባት ያሉት ዋና ፀኃፊው አንቶኒዮ ጉቴሬዝ አፍሪካ ድምፃ እንዲሰማ እና በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንድታገኝ ጥረታቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉም ገልፀዋል።

ከአፍሪካ ጋር በሶስት ጉዳዮች ላይ ትኩረት ሰጥተን እንሰራለን ያሉት ዋና ፀኃፊ የአህጉሪቱ ሰላም ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ መሆኑንም ተናግረዋል።

የአፍሪካ የሀይል ዘርፍ እንዲያድግ በትበብር እንሰራለን ያሉት ጉቴሬዝ አፍሪካውን ከማዕድን ሀብታቸው ተጠቃሚ መሆን አለባቸው ከዚህ በላይ ብዝበዛ ይብቃም ብለዋል።

በአሰግድ ኪዳነማሪያም

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review