AMN ሚያዝያ 30/2018 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት በ5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባኤ የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የሥራ አመራር ቦርድ አባላትን ዕጩዎች ሹመት አጽድቋል፡፡የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክን አቅም እና ተደራሽነት ይበልጥ ለማጠናከር በቀረበዉ ሹመት መሰረት ፡
1ኛ. ክቡር አቶ አቶ ሞገስ ባልቻ-የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ
አቶ ሞገስ ባልቻ በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን ማስተርስ አላቸው፤
በቀድሞ ደቡብ ክልል የየም ዞን ፋይናንስ ጽ/ቤት ሀላፊ፣ የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ሃላፊ፣ የክልሉ ዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ዋና ሃላፊ፣ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ሚኒስትር ሆነው አገልግለዋል ። አሁን ደግሞ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ዋና ሀላፊ ሆነው እያገለገሉ ያሉ፣ አቶ ሞገስ የካበተ የአመራር እና ተቋም ግንባታ ልምድ ያላቸው መሪ ናቸው።
2ኛ. ነብዩ ባዬ(ረዳት ፕሮፌሰር)- የስራ አመራር ቦርድ አባል
ነብዩ በቴአትር ጥበባት የመጀመሪያ ዲግሪ፣ በሥነፅሁፍ ሁለተኛ ዲግሪ፣ በአፍሪካ ጥናት(ሚዲያ፣ ባህል እና ጥበባት) ሦስተኛ ዲግሪ በማጠናቀቅ ላይ ናቸው። ከሃያ አመታት በላይ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከመምህርነት እስከ ኮሌጅ ዲንነት አገልግለዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ዋና ዳይሬክተር፣ የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ኃላፊ፣ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ፣ ሆነው አገልግለዋል አሁን የባህል እና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ናቸው።ከሃያ በላይ የቴአትር እና የፊልም ስራዎች በድርሰት፣ በትወና እና ዝግጅት ሰርተዋል። የተለያዩ ተቋማት የቦርድ ሰብሳቢ እና አባል በመሆን እያገለገሉ ይገኛሉ።
3ኛ. ሰለሞን ካሳ- የስራ አመራር ቦርድ አባል
አቶ ሰለሞን የመጀመሪያ ዲግሪአቸውን በኮምፒውተር ሳይንስ፣ ሁለተኛ ዲግሪ ደግሞ በቴክኖሎጂ ማኔጅመንት ከአሜሪካው ጆርጅ ዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ አላቸው። ሰለሞን ካሳ -ከ17 ዓመታት በላይ ዓለም አቀፍ የሥራ ልምድ ያላቸው፥ ታዋቂ የቴክኖሎጂ አማካሪ፣ ስትራቴጂስት፣ የሚዲያ ባለሙያ፣ አሰልጣኝ ነው።በታዋቂው የዴሎይት (Deloitte USA) አማካሪ ተቋም ውስጥ በከፍተኛ የቴክኖሎጂ አማካሪነት የሰሩ በጤና ጥበቃ፣ በዘላቂ ልማት፣ በአቪዬሽን፣ በፋይናንስ እና በመንግሥት ዘርፎች የብዙ ሚሊዮን ዶላር የቴክኖሎጂ ፕሮጀክቶችን በኃላፊነት የመሩ፥ ከአማካሪነት ሥራ በተጨማሪ፣ ሰለሞን በኢቢኤስ (EBS) ቴሌቪዥን ከፍተኛ ተወዳጅነት ባለው “ቴክቶክ ከሰለሞን ጋር” (TechTalk With Solomon) ፕሮግራም አዘጋጅና አቅራቢ ናቸው።
4ኛ. ዶ/ር ሚኤሳ ኤለማ ሮቤ-የስራ አመራር ቦርድ አባል
ዶ/ር ሚኤሳ በፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት የዶክትሬት ድግሪ አላቸው። የአዳማ ከተማ መንግሥት ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት ሃላፊ፣ የሻሸመኔ ከተማ ምክትል ከንቲባ፣ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ሀላፊ፣ እንዲሁም በከተማ አስተዳደሩ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ ሀላፊ ሆነው ያገለገሉ፤ አሁን ደግሞ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል የህዝብ ግንኙነትና ሚዲያ ዘርፍ ሀላፊ ሆነው እያገለገሉ የሚገኙ ስሆን በተግባቦት እና ሚዲያ ስራ የካበተ ሞያና ልምድ ያላቸው መሪ ናቸው።ዶ/ር ሚኤሳ ከመደበኛ ስራቸው ጎንለጎን በከተማ እና ሀገር አቀፍ ጉዳዮች ፣ እንዲሁም የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅምን የተመለከቱ በርካታ ጽሁፎችን በዲጂታል ህትመት ሚዲያዎች የሚፅፉ የፖለቲካ ሳይንስ ባለሞያ ናቸው።
5ኛ. ወ/ሮ ልእልት ግደይ – የስራ አመራር ቦርድ አባል
ልእልት ግደይ የመጀመሪያ ዲግሪ በኢትዮጲያ ቋንቋዎች እና ስነ ፅሁ
ሁለተኛ ዲግሪ በተግባራዊ ስነልሳ የኢትዮጲያ ቋንቋዎችን ማስተማር አላቸው። ከ18 ዓመት በላይ በመምህርነት፥ በርእሰ መምህርነት፥ በአራዳ ክ/ከተማ በምክትል ስራ አስፈፃሚ፥ በአዲስ አበባ ምክርቤት የመሰረተልማት እናትራንስፓርት ጉዳዬች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢነት፥ የአዲስ አበባ ህ/ስራ ኮምሽን ኮምሽነር ሆነው አገልግለዋል ። አሁን ላይ የልደታ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ናቸው።
6ኛ. ወ/ሮ ዘሃራ መሃመድ -የስራ አመራር ቦርድ አባል
ወደ/ሮ ዘሃራ የመጀመሪያ ዲግሪ አላቸው። የአዲስ አበባ ንግድ ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ፥የተለያዩ የበጎ አድራጎት ስራ የሚሰሩ፥ እንዲሁም ነጋዴ ናቸው።