AMN የካቲት 08 ቀን 2018 ዓ.ም
41ኛው የዙሪክ ሲቪያ ማራቶን ዛሬ ተካሂዷል፡፡ በወንዶች ኢትዮጵውያን አትሌቶች ተከታትለው በመግባት አሸንፈዋል፡፡
የ2020ው የለንደን ማራቶን አሸናፊው ሹራ ቂጣታ ከአምስት ዓመታት በኋላ ወደ ድል ተመልሷል፡፡
የ2022ቱ የሲቪያ ማራቶን አሸናፊው አስራር አብዱራህማን በፎቶ አጨራረስ ተቀድሞ ሁለተኛ ደረጃን አግኝቷል፡፡
ሁለቱም አትሌቶች የገቡበት ሰዓት 2:03:59 ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
ሌላው ኢትዮጵያዊ ደጀኔ ኃይሉ ሶስተኛ ደረጃን ይዞ ውድድሩን አጠናቋል፡፡
ኬንያዊ ጀስተስ ኪፕኮሪር አራተኛ ደረጃን ሲይዝ ፣ ካፒታል ደገፋ ፣ ጽዳት አበጀ ፣ ፈይሳ ሙሉ እና ልመንህ ጌታቸው ከአምስተኛ እስከ ስምንተኛ ያለውን ደረጃ ይዘው ውድድራቸውን ጨርሰዋል።
በሴቶቹ አትሌት ሙላት ተክሌ ሶስተኛ ደረጃን አግኝታ ውድድሯን አጠናቃለች፡፡ ፊልንዳዊቷ አሊሳ ቫይኒዮ ውድድሩን አሸንፋለች፡፡ የገባበችበት 2:20 :39 ሰዓት የሀገሪቱ የምንጊዜውም ፈጣን ሰዓት ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ ኬንያዊቷ ቢትሪስ ጄፕቺርቺር ሁለተኛ ሆና ውድድሯን አጠናቃለች፡፡
መካሄድ ከጀመረ 41 ዓመታት ያስቆጠረውን የሲቪያ ማራቶን በወንዶች ደረሳ ገለታ በሴቶች መገርቱ ዓለሙ የቦታውን ፈጣን ሰዓት መያዛቸው ይታወቃል፡፡
በታምራት አበራ