ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመዲናዋ የተካሄዱት ጉባዔዎች ከወትሮው በተለየ በታላቅ ድምቀትና ስኬት እንዲጠናቀቁ የላቀ ትብብርና ታጋት ያደረጉ አካላትን በሙሉ አመሰገኑ

You are currently viewing ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመዲናዋ የተካሄዱት ጉባዔዎች ከወትሮው በተለየ በታላቅ ድምቀትና ስኬት እንዲጠናቀቁ የላቀ ትብብርና ታጋት ያደረጉ አካላትን በሙሉ አመሰገኑ

AMN የካቲት 8/2018

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመዲናዋ የተካሄዱት ጉባዔዎች ከወትሮው በተለየ በታላቅ ድምቀትና ስኬት እንዲጠናቀቁ የላቀ ትብብር እና ትጋት ያደረጉ አካላትን በሙሉ አመሰግነዋል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልዕክት 39ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ እና 2ኛው የጣሊያን- አፍሪካ ጉባኤ ከወትሮው በተለየ ታላቅ ድምቀትና ስኬት ተጠናቅቀዋል ብለዋል።

ጉባኤዎቹ በውቧ መዲናችን አዲስ አበባ ፍጹም ስኬታማ በሆነ መንገድ እንዲካሄዱ መደረጉ፤ እንግዶቻችን የኢትዮጵያዊያንን ለዘመናት የዘለቀ እንግዳ ተቀባይነት እንዲሁም የመዲናችንን አስደናቂ ለውጥና ለጉባኤዉም ትልቅ ሞገስ ሆኗል።

መላው የከተማችን ነዋሪዎች ላሳያችሁት እንግዳ አክባሪነት፣ ትዕግስትና አጋርነት ፣ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ለሰጣችሁት ጥራት ያለው እና ቀልጣፋ አገልግሎት፤ ከተማችንን ሁሌም አዲስ ገፅታ እና መንፈስ በማላበስ ይህ ጉባኤ እንዲሳካ ላደረጋችሁ የከተማችን አመራሮች እና ሰራተኞች፤ በተለይም ከካዛንቺስ እስከ ቦሌ ብራስ ያላችሁ የግል ተቋማትና ግለሰቦች ለሌት ተቀን ትጋታችሁና ቀና ትብብራችሁ፤ እንዲሁም ከነዋሪው ጋር በመቀናጀት በቁርጠኝነት ለሠራችሁ የጸጥታ አካላት በራሴና በከተማ አስተዳደሩ ስም ላቅ ያለ ምስጋናዬን አቀርባለሁ ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት አስተላልፈዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review