AMN – የካቲት 10/2018 ዓ.ም
የቱርክዬ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ረጀብ ጠይፕ ኤርዶዋን፣ የመላው ጥቁር ሕዝቦች ኩራት በሆነው የዓድዋ ድል መታሰቢያ ተገኝተው፤ ለጥቁር ሕዝቦች ነፃነት ዋጋ የከፈሉ ጀግኖች መታሰቢያ ሐውልት ሥር የአበባ ጉንጉን ማኖራቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል።
ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ ፕሬዝዳንት ረጀብ ጠይፕ ኤርዶዋን በምድረ ቀደምቷ ኢትዮጵያና በውቧ መዲናችን አዲስ አበባ የሚኖራቸው ቆይታ ፍሬያማ እንዲሆን በራሴና በከተማ አስተዳደሩ ስም ከልብ እመኛለሁ ብለዋል።