በመዲናዋ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ጥራት ለማሻሻልና ከገበያው ፍላጎት ጋር እንዲጣጣም ለማድረግ የተለያዩ የማሻሻያ ሥራዎች እየተከናወኑ ነዉ

You are currently viewing በመዲናዋ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ጥራት ለማሻሻልና ከገበያው ፍላጎት ጋር እንዲጣጣም ለማድረግ የተለያዩ የማሻሻያ ሥራዎች እየተከናወኑ ነዉ

AMN- የካቲት 13/2018 ዓ.ም

በመዲናዋ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ጥራት ለማሻሻልና ከገበያው ፍላጎት ጋር እንዲጣጣም ለማድረግ የተለያዩ የማሻሻያ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆናቸዉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ አስታወቀ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ለ16ኛ ጊዜ የሚከበረውን የቴክኒክና ሙያ ሳምንትን ምክንያት በማድረግ የሰልጣኞች የክህሎት ውድድር በማካሔድ ላይ ይገኛል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ሚዴቅሳ ከበደ፣ የውድድሩ ዓላማ ወጣቶች ያላቸውን የፈጠራ አቅም በማውጣት ወጪ ቆጣቢ ሀገር በቀል ቴክኖሎጂዎችን ለመፍጠር የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በውድድሩ ከአሁን በፊት በ14 ኮሌጆች 509 ሰልጣኞች ተወዳድረው ያሸነፉት 123 ሰልጣኞች በ6 ክላስተር እንደሚወዳደሩ ገልጸዋል፡፡

ይህም ተማሪዎች በንድፈ ሐሳብ ብቻ ሳይወሰኑ በተግባር የታገዘ ሥልጠና እንዲያገኙና በዘመናዊ መሣሪያዎች እንዲለማመዱ ዕድል መፍጠሩን ገልጸዋል።

የቢሮው ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ ዳግማዊት ግርማ፣ የክህሎት ውድድሩ በሁሉም ዘርፍ ብቁ እና ተወዳዳሪ የሆነ ትውልድ መገንባቱን ለማረጋገጥ እንደሚያስችል ተናግረዋል፡፡

በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሥልጠና ጥራቱን ለማሻሻልና ከገበያው ፍላጎት ጋር ለማጣጣም የተለያዩ የማሻሻያ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን አንስተዋል።

ተወዳዳሪዎች በበኩላቸው፣ ውድድሩ ያላቸውን እምቅ አቅም ለማውጣት እንደሚያስችላቸው ገልጸዋል፡፡

በታምራት ቢሻው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review