የአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን ከታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ያዘጋጁት የአምስት ኪሎ ሜትር ሩጫ በእንጦጦ ፓርክ ተካሄደ

You are currently viewing የአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን ከታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ያዘጋጁት የአምስት ኪሎ ሜትር ሩጫ በእንጦጦ ፓርክ ተካሄደ

AMN – የካቲት 14/2018 ዓ.ም

የአዲስ አበባን ቱሪዝም ለማስተዋወቅ ያግዛል የተባለው የንግድ ባንክ የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ በእንጦጦ ፓርክ ተካሂዷል፡፡

በእንጦጦ ፓርክ ውስጥ ያለውን የአዲስ አበባን ቱሪዝም ለማህበረሰቡ ለማስተዋወቅ እና በስፖርታዊ እንቅስቃሴ ተሳትፎ ጤንነቱን እንዲጠብቅ ታስቦ መዘጋጀቱን የአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን ኮሚሽነር ሁንዴ ከበደ ለኤ ኤም ኤን ተናግረዋል፡፡

ባለፉት ዓመታት በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ምቹ የስፖርት መሰረተ ልማቶች መገንባታቸውን ያስታወሱት ኮሚሽነር ሁንዴ ፣ እነዚህን መሰረት ልማቶች ጥቅም ላይ ለማዋል መሰል ውድድሮችን ማዘጋጀት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡

ተሳታፊዎች በበኩላቸው ለሩጫ ምቹ በሆነው እንጦጦ ፓርክ እንደዚህ ዓይነት መርሃ ግብር መዘጋጀቱ ጤንነታቸውን ከመጠበቅ ባሻገር የመዝናኛ አማራጭ እንደሆናቸው ገልጸዋል፡፡

የአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን ከአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ጋር በመተባበር በቅርቡ የማህበረሰብ ዓቀፍ የብስክሌት ጉዞ ውድድር ማካሄዱ የሚታወስ ነው፡፡

በታምራት አበራ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review