AMN-ሐምሌ 9/2018 ዓ.ም

ኢትዮጵያ ቡና የቀድሞ አሰልጣኙ ገብረመድህን ሃይሌ መሾሙን ዛሬ ይፋ አድርጓል።
ለቀጣይ ሁለት ዓመታት ለመቆየት የተስማማው አሰልጣኙ ከ16 ዓመታት በኃላ ወደ ቡና የተመለስኩት ለክለቡ ታሪክ ለመስራት ነው ብሏል::

ከ20 ቀናት በኋላ በይፋ ስራ የሚጀምርው እሰልጣኙ ጠንካራ ቡድን በመገንባት በደጋፊው በጥብቅ የሚፈለገውን የሊጉን ዋንጫ ለማሳካት እንዳሰበ ገልጿል::
የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ከፍተኛ አመራሮች በቡና ስም ጠንካራ የሆነ ተቋም እንዲኖር እንጂ ውጤታማ ያልሆነ ጉዞ ስለማይመጥን አስፈልጊውን ድጋፍ እናደርጋለን ብለዋል::
በዮናስ ሞላ