ከንቲባ አዳነች አቤቤ 5ኛዉን የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አስጀመሩ

You are currently viewing ከንቲባ አዳነች አቤቤ 5ኛዉን የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አስጀመሩ
  • Post category:ኢኮኖሚ

AMN የካቲት 14/2018

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት ዛሬ በከተማችን ለ5ኛ ጊዜ የሚካሄደውን የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ “ኢትዮጵያ ታምርት፣ አዲስ አበባ ትበልፅግ” በሚል መሪ ቃል በይፋ አስጀምረናል ብለዋል፡፡

ንቅናቄው ባለፉት የለውጥ ዓመታት በተለያዩ ማነቆዎች ተዘግተው የነበሩ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ዳግም ወደ ምርታማነት በመመለስ፤ የፋይናንስና የማምረቻ ቦታዎችን በማመቻቸት፤ የገበያ ትስስር በመፍጠር እንዲሁም የእውቀትና የቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲኖር በማድረግ ረገድ አስተዳደራችን የወሰዳቸው እርምጃዎች ፍሬ እያፈሩ መሆናቸውን የተመለከትንበት ነው ብለዋል፡፡

በዚህም በዘርፉ በከተማችን እየተከናወኑ ባሉ ተግባራት ተጨባጭ ለውጥ ማስመዝገብ ችለናል።

በተለይም በተኪ ምርቶች እድገት ረገድ የአገር ውስጥ ምርት ተጠቃሚነት ባህል እያደገ መጥቷል። አምራቾች በቀጣይም በየዕለቱ በምርት ጥራት ላይ በመላቅ ተወዳዳሪነታችሁን እያሳደጋችሁ እንድትሄዱ አደራ ለማለት እወዳለሁ ሲሉ ገልጸዋል፡፡

የተለያዩ የጨርቃጨርቅ (ቴክስታይል)፣ የሕክምና፣ የቆዳና የቆዳ ውጤቶች እንዲሁም የኤሌክትሮኒክስ ምርቶች በስፋት የቀረቡበት ይህ ንቅናቄ፤ ለሚቀጥለው አንድ ሳምንት እጅግ ውብና ከሁሉም የከተማው ክፍል ለትራንስፖርት አመቺ ሆኖ በተገነባው በአዲስ አበባ ኮንቬንሽን ሴንተር የሚቆይ ይሆናል።

መላው የከተማችን ነዋሪዎች የከተማችን አምራች ኢንዱስትሪዎች ያመረቷቸውን ውጤቶች እንድትጎበኙና እንድትሸምቱ ጥሪዬን አቀርባለሁ ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review