AMN- ሐምሌ 22/2018 ዓ.ም
የፊፋ የዲሲፕሊን ኮሚቴ የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች ላይ የዲሲፕሊን ምርመራ መጀመሩን ይፋ አደረገ።
የእግርኳስ የበላይ ጠባቂ የሆነው ተቋም በዓለም ዋንጫ ፍፃሜ አርጀንቲና በስፔን 1ለ0 ተሸንፋ ዋንጫውን ካጣች በኋላ የተወሰኑ ተጫዋቾች የፈጠሩትን አምባጓሮ እየመረመረ እንደሆነ አስታውቋል።
የአርጀንቲና ተጫዋቾች ናሁል ሞሊና (በሁለት ጥፋት) ፣ ሊአንድሮ ፓሬዴዝ (በሦስት ጥፋት) እንዲሁም ረዳት አሰልጣኙ ሮቤርቶ አያላ (በአንድ ጥፋት) የፊፋን አንቀፅ 14 ተላልፈዋል በሚል ምርመራ ተጀምሮባቸዋል።
የአርጀንቲናው ሌላኛው ተጫዋች ቲያጎ አልማዳ እና የስፔኑ አማካይ ጋቪ ሌላ ምርመራ የሚደረግባቸው ተጫዋቾች ነው።
ምርመራው ሲጠናቀቅ እንደጥፋታቸው እስከ ሦስት ጨዋታ ሊቀጡ እንደሚችሉ ቢቢሲ ስፖርት ዘግቧል።