AMN – የካቲት 17/2018 ዓ.ም
በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ የመልስ መርሐግብር ዛሬ አራት ጨዋታዎች ይከናወናሉ።
በመጀመሪያው ጨዋታ ወደ ኖርዌይ አቅንቶ በቦዶ/ግሊምት 3ለ1 የተሸነፈው ኢንተር ሚላን በሜዳው ጄሴፔ ሜይዛ ይጫወታል።
የሴሪ አው መሪ ውጤቱን ለመቀልበስ መረቡን ሳያስነካ ከሁለት በላይ ግቦችን ማስቆጠር ይጠበቅበታል።
የአዘርባጂያውን ካራባግ 6ለ1 በመርታት የማለፍ ዕድሉን በእጅጉ ያሰፋው ኒውካስትል ዩናይትድ የመልሱን ጨዋታ በሴንት ጀምስ ፓርክ ያደርጋል።
በጨዋታው ኤዲ ሃው ለወሳኝ ተጫዋቾቻቸው እረፍት ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ከሜዳው ውጪ የግሪኩን ኦሊምፒያኮስ 2ለ0 መርታት የቻለው ባየር ሊቨርኩሰን ውጤቱን ለማስጠበቅ ወደ ሜዳ ይገባል።
የጀርመኑ ክለብ በሜዳው ባይ አሬና እንደመጫወቱ በመጀመሪያ ጨዋታ ያስመዘገበውን ውጤት ለማስጠበቅ ይቸገራል ተብሎ አይጠበቅም።
ከላይ የተጠቀሱት ሦስቱም ጨዋታዎች ምሽት 5 ሰዓት ላይ ይጀምራሉ።
ምሽት 2:30 አትሌቲኮ ማድሪድ በዋንዳ ሜትሮ ፖሊታኖ የቤልጂየሙን ክለብ ብሩጅን ይገጥማል።
በድራማ የታጀበው የሁለቱ ክለቦች የመጀመሪያ ጨዋታ 3ለ3 መጠናቀቁ ይታወሳል።
በሸዋንግዛው ግርማ