ለነገዋ የሴቶች ተሃድሶና እና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል ስልጠናቸውን ላጠናቀቁ ሴቶች የብቃት መመዘኛ ፈተና ሰጠ

You are currently viewing ለነገዋ የሴቶች ተሃድሶና እና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል ስልጠናቸውን ላጠናቀቁ ሴቶች የብቃት መመዘኛ ፈተና ሰጠ

AMN የካቲት 19/2018

ለነገዋ የሴቶች ተሃድሶና እና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል በ4ኛው ዙር ከ1 ሺህ በላይ ሴቶችን በማሰልጠን ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ የብቃት መመዘኛ ፈተና በመስጠት ፈተናውን ያለፉትን ለምረቃ እያዘጋጀ መሆኑን አስታውቋል።

ማዕከሉ ሴቶቹን በኪነጥበብ ዘርፍ ለማብቃት በተለያዩ አቅጣጫዎች ስልጠና ሲሰጥ መቆየቱን ገልጿል።

ሴቶችን በኪነጥበብ ስራዎች ለማብቃት የአዲስ አበባ ባህልና ኪነጥበብ ቢሮ ከማዕከሉ ጋር በቅንጅት በመስራቱ ውጤታማ ስራ መከናወኑ ተጠቁሟል። የአዲስ አበባ ባህልና ኪነጥበብ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ወይዘሮ ሉባባ ጃማል እንደ ለነገዋ የሴቶች ተሃድሶና እና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል ባሉ የሰብአዊነት ስራ የሚሰሩ ተቋማትን ማገዝ የማህበረሰባችን ግዴታ ነው ብለዋል።

ወይዘሮ ሉባባ አክለውም፣ የቀረቡት የኪነጥበብ ስራዎች በተለያዩ ማህበራዊ እና ስነ-ልቦናዊ ችግሮች ውስጥ የነበሩ ሴቶች እንዲያገግሙና ራሳቸውን እንዲመለከቱ የሚያደርጉ መሆኑን አስገንዝበዋል።

የማዕከሉ የእንክብካቤ እና ድጋፍ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወይዘሮ ጥሩወርቅ ደበበ በበኩላቸው፤ ሰልጣኝ ሴቶቹን በተለያዩ የኪነጥበብ አይነቶች ሲያበረታቱና ሲያስተምሩ መቆየታቸውን በመጥቀስ፣ የአዲስ አበባ ባህልና ኪነጥበብ ቢሮ ላበረከተው ድርሻ ምስጋና አቅርበዋል።

በአጠቃላይ በ4ኛው ዙር ከ1ሺህ በላይ ሴቶች በማዕከሉ የሚሰጠውን ስልጠና ሲከታተሉ የቆዩ ሲሆን፣ ከእነዚህ ውስጥ ከ900 በላይ የሚሆኑት በማዕከሉ የተሰጠውን የብቃት መመዘኛ ፈተና በማለፍ ለምረቃ መዘጋጀታቸውን አስታውቀዋል። እነዚህ በተለያዩ ሙያዎች የሰለጠኑ ሴቶች የስራ እድል እንዲያገኙ ከተለያዩ ተቋማት ጋር የትስስር ስራ እየተሰራ መሆኑም ተገልጿል።

በበየነ ታደሰ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review