የኢትዮጵያ ካራቴ ብሔራዊ ቡድን አራት የወርቅ ሜዳሊያዎችን አሸነፈ

AMN ግንቦት 23/ 2018 ዓ.ም

በ2026 የምስራቅ አፍሪካ ካራቴ ሻምፒዮና ላይ እየተሳተፈ የሚገኘው የኢትዮጵያ ካራቴ ብሔራዊ ቡድን በመጀመሪያው ቀን ብቻ ዘጠኝ ሜዳሊያዎችን አሳክቷል።

​በኬንያ አስተናጋጅነት እየተካሄደ ባለው ውድድር ብሔራዊ ቡድኑ በወንዶች ከ75 ኪሎ ግራም በታች እና ከ53 ኪሎ ግራም በታች ፣ እንዲሁም በሴቶች ካታ እና በቡድን ኩሚቴ ባሳየው ብቃት አራት የወርቅ ሜዳሊያዎችን አሸንፏል።

​በተጨማሪም በወንዶች ከ67 ኪሎ ግራም በታች እና በቡድን ካታ ውድድር ሁለት የብር ሜዳሊያዎች ተገኝተዋል።

​በወንዶች ካታ ፣ ከ60 ኪሎ ግራም በታች እና ከ84 ኪሎ ግራም በታች ሦስት የነሐስ ሜዳሊያዎች የተመዘገበባቸው ሌሎች ዘርፎች ናቸው።

አምስት ሀገራት እየተሳተፉበት የሚገኘው የምስራቅ አፍሪካ የካራቴ ሻምፒዮና ውድድር ዛሬ ፍጻሜውን እንደሚያገኝ የባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review