AMN- የካቲት 20/2018 ዓ.ም
የ2025/26 የውድድር ዓመት የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ውድድር 16 ክለቦች የሚፋለሙበት የጥሎ ማለፍ ዙር ላይ ደርሷል። የእነዚህ ክለቦች እጣ ድልድልም ዛሬ ይፋ ይሆናል።
በሊግ ምዕራፍ ከ1-8ኛ ደረጃ ይዘው የጨረሱ ቡድኖች ቀድመው ማለፋቸው ይታወሳል። ከ9-24 የጨረሱ ቡድኖች ደግሞ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ አድርገው አሸናፊ ስምንት ቡድኖች ተለይተዋል።
እነዚህ 16 ቡድኖች ናቸው 8 ሰዓት ላይ በሚከናወነው ድልድል ተጋጣሚዎቻቸውን የሚለዩት።
ማን ከማን ይገናኛል የሚለው በጉጉት ይጠበቃል። በሊግ ምዕራፉ ስምንቱንም ጨዋታዎች በማሸነፍ በቀዳሚነት ያጠናቀቀው አርሰናል ቀለል ያለ ቡድን የሚያገኝ ይመስላል።
የሰሜን ለንደኑ ክለብ በዕጣ ድልድሉ ባየር ሊቨርኩሰን ወይም አታላንታን ያገኛል።
የባለፈው ውድድር ዓመት አሸናፊው ፓሪሰን ዠርማ ፈታኝ ተጋጣሚ ይጠብቀዋል። የፈረንሳዩ ክለብ ባርሰሎና አልያም ቼልሲን ለመግጠም ይገደዳል።
ሊቨርፑል ከአትሌቲኮ ማድሪድ እና ከጋላታሳራይ ከአንዱ ጋር ይፋለማል።
የ15 ጊዜ የቻምፒየንስ ሊግ አሸናፊው ሪያል ማድሪድ ማንችስተር ሲቲ ወይም ስፖርቲንግ ሊዝበንን ያገኛል።
በዛሬው ዕጣ ድልድል በሩብ ፍፃሜ እና ግማሽ ፍፃሜ ማን ከማን ሊገናኝ እንደሚችል አብሮ ይፋ ይሆናል።
በሸዋንግዛው ግርማ