ለትግራይ ሕዝብና ወጣቶች ያስተላለፉት መልዕክት፡-
“የትግራይ ሕዝብ ከጦርነት ይልቅ ሰላምና ልማት ይገባዋል” ብለዋል።
ወጣቶች የስልጣን ባለቤት እንዲሆኑና በአሮጌ አስተሳሰብ ለጦርነት ከሚገፋፏቸው አካላት ራሳቸውን እንዲጠብቁ መክረዋል።
መንግሥት በትግራይ ክልል ሰላም እንዲሰፍንና ዳግም ጦርነት እንዳይከሰት ጽኑ ፍላጎት እንዳለውና ለዚህም ማንኛውንም መስዋዕትነት እንደሚከፍል አረጋግጠዋል።
የሰሜኑን ጦርነት መንስኤዎች በተመለከተ
ሕወሓት ከ50 ዓመት በፊት በነበረ ኋላቀር አስተሳሰብ የታሰረ መሆኑና ለውጥን ለመቀበል አለመፈለጉ። ዓለም በቴክኖሎጂና በ”ፕራግማቲዝም” በምትመራበት ዘመን፣ ድርጅቱ በአሮጌው መንገድ ለመጓዝ መሞከሩ ለግጭት ዳርጎታል።
ቆሞ ቀሩ ኃይል “ኢትዮጵያ ትፈርሳለች” የሚል የተሳሳተ ስጋት በመዝራት የለውጡን ኃይል እንደ ጠላት ማየቱ።
የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ተግባራዊነት በተመለከተ ፡-
መንግሥት የትግራይ ሕዝብ ሰላም እንዲያገኝ ባንክ፣ መብራትና ቴሌኮም የመሳሰሉ አገልግሎቶችን በፍጥነት እንዲመለሱ ማድረጉን ገልጸዋል።
ሆኖም ቆሞ ቀሩ ቡድን ስምምነቱን “መርጦ የመተግበር” ዝንባሌ እያሳየ መሆኑን ተችተዋል። በተለይም ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ውሳኔ አለማክበሩን ጠቅሰዋል።
ድርጅቱ ለልማት የተመደበውን በጀት ለጦርነት ዝግጅትና ለታጣቂዎች ቀለብ እየዋለ መሆኑን ገልጸው፣ ይህም በትግራይ ሕዝብ ላይ ተጨማሪ መከራ እያመጣ መሆኑን አስገንዝበዋል።
በጦርነቱ ወቅት የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በተመለከተ፡-
ጦርነት ሁልጊዜም አስከፊ ገጽታ እንዳለው ገልጸው፣ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ የሽግግር ፍትሕ (Transitional Justice) አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል።
ይህ ሂደት ከፖለቲካ ወገንተኝነት ነፃ በሆነ መንገድ ሊካሄድ እንደሚገባውና ወንጀል የፈጸሙ አካላት በሕግ መጠየቅ እንዳለባቸው ገልጸዋል።
የኤርትራ መንግሥት (ሻዕቢያ) ሚና
በጦርነቱ ወቅት የኤርትራ ጦር ያደረገው ድጋፍ የሚታወስ መሆኑን ጠቅሰዋል።
ሆኖም በጦርነቱ ሂደት የተፈጸሙ ማናቸውም ዓይነት ጥፋቶች፣ ግድያዎችና ዘረፋዎች (በተለይም በአክሱም፣ ዓድዋና ሽሬ አካባቢዎች) የማይቀበሉትና የሚወገዝ ተግባር መሆኑን በግልጽ አስታውቀዋል።
መንግሥት ማንኛውንም የውጭ ኃይል ጣልቃ ገብነት እንደሚቃወምና የሀገርን ሉዓላዊነት ለማስከበር እንደሚሠራ ገልጸዋል።