ድሬ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በስድስት ወራቶች ውስጥ ከ23 ሺ በላይ ተገልጋዮችን አስተናግዷል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

You are currently viewing ድሬ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በስድስት ወራቶች ውስጥ ከ23 ሺ በላይ ተገልጋዮችን አስተናግዷል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

AMN የካቲት 29/2018 ዓ.ም

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ድሬ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ስራ ከጀመረበት ስድስት ወራቶች ውስጥ በአጠቃላይ ከ23 ሺ በላይ ተገልጋዮችን አስተናግዷል ሲሉ ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት ድሬ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት፤ በውስጡ 10 ተቋማት ይዞ 73 የሚሆኑ አገልግሎቶችን ለዜጎች በመስጠት ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡

አንድ ማዕከሉ ተገልጋዬችን የሚያስተናግዱ 96 ካውንተሮች እንዲኖሩት ተደርጎ የተደራጀ ነው።

ማዕከሉ ስራ ከጀመረበት ስድስት ወራቶች ውስጥ በአጠቃላይ ከ23 ሺ በላይ ተገልጋዮችን አስተናግዷል። ከፍ ብሎ የተጀመረውን የተቀላጠፈ የዲጅታል አገልግሎት ይበልጥ ለማስፋት አቅዶም እየሠራ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review