AMN- መጋቢት 03/2018 ዓ.ም
“የመደመር መንግሥት ለሃይማኖት ተቋማት ያለው እይታ፣ አስተዳደራዊ መርሆዎች፣ ያጋጠሙ ችግሮችና የመፍትሔ አቅጣጫዎች” በሚል መሪ ሀሳብ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ከሚገኙ የወንጌል አማኞች መሪዎች ጋር የውይይት መድረክ ተካሂዷል።
ውይይቱን የመሩት የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጥላሁን ወርቁ፤ የሃይማኖት ተቋማት ሀገር ወዳድና በሥነ-ምግባር የታነጸ ትውልድ የመቅረጽ ማኅበራዊ ኃላፊነታቸውን በላቀ ደረጃ ሊወጡ እንደሚገባ አሳስበዋል።

በውይይቱ ላይ የተሳተፉት የእምነቱ መሪዎችና አገልጋዮች እንደገለጹት፤ መንግሥት ከምንጊዜውም በላይ ከሃይማኖት ተቋማት ጋር ተቀራርቦ መሥራቱ የሚመሰገን ተግባር ነው።
በተለይም የመደመር እሳቤ ለሃይማኖቶች እኩልነት በሰጠው ትኩረት፣ በቤተ እምነቶች መካከል ያለውን ልዩነት በማጥበብ ረገድ የጎላ ሚና ማበርከቱን በበጎነት አንስተዋል።
አክለውም፣ የወንጌል አማኞች ትውልድን በመልካም ሥነ-ምግባር የመቅረጽና በሕዝቦች መካከል ያለውን የአብሮነት ትስስር የማጠናከር ታሪካዊ ኃላፊነታቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።
በፍቃዱ መለሰ