የአራዳ ፓርክ ዋና ዋና ይዘቶች እና አገልግሎቶች

You are currently viewing የአራዳ ፓርክ ዋና ዋና ይዘቶች እና አገልግሎቶች

AMN – ሚያዝያ 23/2018 ዓ.ም

የአራዳ ፓርክ የቀድሞ ታሪካዊ ቅርሶችን በማደስ እና አዳዲስ ዘመናዊ አገልግሎቶችን በማካተት የተገነባ ነው።

የቅርሶች እድሳት፦ በአካባቢው ያሉ ወደ 700 የሚጠጉ ህንጻዎች ታድሰዋል።

አረንጓዴ ልማት፦ አረንጓዴ ስፍራዎች፣ አበባዎች፣ ዛፎች እና የውሃ ፋፋቴዎች ተካተዋል።

የንግድ ሱቆች፦ ለፒያሳ ልማት ተነሺዎች ቅድሚያ በመስጠት ከ131 በላይ ሱቆች ተገንብተዋል።

መዝናኛ እና ስፖርት፦ የሥዕል ጋለሪ፣ የስጦታ እቃ መሸጫ እና በሀገራችን የመጀመሪያው የሆነው የስፖርት አሬና ተገንብቷል።

አዳራሾች እና ፕላዛዎች፦ እስከ 2ሺህ ሰው መያዝ የሚችል ትልቅ አዳራሽ እና 6 ትናንሽ አዳራሾች። እስከ 10ሺህ ሰው ሊያስተናግዱ የሚችሉ ሁለት ትላልቅ ፕላዛዎች።

መንገዶች፦ 5 ኪሎ ሜትር የሩጫ እና 5 ኪሎ ሜትር የሳይክል መንገድ። 6 ኪሎ ሜትር የእግረኛ መንገድ።

ለህጻናት፦ 5 የመጫወቻ ስፍራዎች (አራቱ በነጻ የሚያገለግሉ ናቸው)፡፡ በተጨማሪም ስለ አገልግሎት እና ሀገር ፍቅር በጨዋታ መልክ የሚማሩባት ትንሿ ከተማ ተገንብታለች።

መኪና ማቆሚያ፦ በአንድ ጊዜ 131 እና ከዚያ በላይ መኪናዎችን መያዝ የሚችል የመሬት ውስጥ መኪና ማቆሚያ ያካተተ ነው።

በታደሠ ሽፈራው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review