AMN መጋቢት 8/2018 ዓ.ሞ
በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ጦርነት በአስቸኳይ ሊቆም እንደሚገባ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ጥሪ አቀረቡ።
ዋና ጸሐፊው አንቶኒዮ ጉተሬዝ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ስብሰባ ላይ:- በመካከለኛው ምስራቅ እየተባባሰ የመጣው ግጭት እንዲቆም እና የዲፕሎማሲ አማራጮች ቅድሚያ እንዲሰጣቸው ጥሪ አቅርበዋል።
ዋና ጸሐፊው በንግግራቸው ወቅት:- የፀጥታው ምክር ቤት ያሳለፋቸው ውሳኔዎች በሙሉ በተግባር ላይ መዋል እንዳለባቸው አጽንኦት ሰጥተዋል።
በተለይም የባህረ ሰላጤው ሀገራት አሁንም ለጥቃት እየተጋለጡ መሆኑን በመጥቀስ፣ ውሳኔ ቁጥር 2817 ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ መከበር እንዳለበት አሳስበዋል።

በመካከለኛው ምስራቅ እየታየ ያለው የኃይል እርምጃ በአስቸኳይ እንዲቆም እና የዲፕሎማሲያዊ ንግግሮች እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል።
“ሁሉም የፀጥታው ምክር ቤት ውሳኔዎች ሊተገበሩ ይገባል፤ ይህም የምክር ቤቱ ተዓማኒነት መለኪያ ነው” ብለዋል።
በወንድማገኝ አሰፋ