AMN መጋቢት 14/2018 ዓ.ም
ኢራን የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ በሁለቱ ሐገራት መካከል ውይይት ተደርጓል ሲሉ የሰጡትን አስተያየት ማስተባበሏ ተዘገበ።
የአሜሪካዉ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ ዩናይትድ ስቴትስ እና ኢራን በመካከለኛው ምስራቅ ያለውን ጸብ ሙሉ በሙሉ ለመፍታት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ንግግር ማድገራቸዉን ገልጸዋል፡፡
እሳቸው እንዳሉት ከሆነ፣ በንግግሩ ምክንያት በኢራን የኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች ላይ ሊሰነዘር ታስቦ የነበረው ጥቃት ለአምስት ቀናት ተራዝሟል። በዚህም ምክንያት የነዳጅ እና የጋዝ ዋጋ ወዲያውኑ መቀነሱ ተዘግቧል።
በሌላ በኩል የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከአሜሪካ ጋር እንዲህ ዓይነት ንግግሮች መደረጋቸውን አስተባብሏል፡፡
ይህም በሁለቱ ወገኖች መካከል “ውጤታማ ውይይቶች” ተካሂዷል ሲሉ ፕሬዝዳንት ትረምፕ የሰጡትን አስተያየት የሚቃረን መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ትረምፕ ቆየት ብለው በሰጡት መግለጫ ደግሞ የጥቃቱ መዘግየት በጥሩ ሁኔታ ከሄደ ጉዳዩን መፍታት እንችላለን ፤ ካልሆነ ግን ጥቃቱ ሊቀጥል ይችላል ብለዋል።
በወንድማገኝ አሰፋ