በኢትዮጵያ የጥላቻ ንግግርና የሀሰተኛ መረጃ ስርጭት በ4 በመቶ መጨመሩ ተገለጸ

You are currently viewing በኢትዮጵያ የጥላቻ ንግግርና የሀሰተኛ መረጃ ስርጭት በ4 በመቶ መጨመሩ ተገለጸ

AMN- መጋቢት 18/2018 ዓ.ም

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ባለፈው አንድ ዓመት የጥላቻ ንግግርና የሀሰተኛ መረጃ ስርጭት በ4 በመቶ መጨመሩን አስታወቀ።

ባለሥልጣኑ የጥላቻ ንግግርና የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን አስመልክቶ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፣ በ5 ክልሎችና በ2 የከተማ አስተዳደሮች ላይ የተደረገ የዓመት ጥናትን ይፋ አድርጓል።

የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሃይማኖት ዘለቀ እንደገለጹት፣ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የሚንቀሳቀሱ አክቲቪስቶች ችግሩን በማባባስ ረገድ ቀዳሚውን ድርሻ ይወስዳሉ።

በተለይም 27 በመቶ የሚሆነው የጥላቻ ንግግር የሚተላለፈው በእነዚሁ አክቲቪስቶች አማካኝነት መሆኑን በጥናቱ መረጋገጡን ዋና ዳይሬክተሯ ተናግረዋል።

ወ/ሮ ሃይማኖት አክለውም፣ ይህ ችግር የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የዓለም ስጋት እየሆነ መምጣቱን ጠቅሰው፣ ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ ስርጭቱን ለመግታት በርካታ ሥራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

በመሆኑም የሚመለከታቸው አካላትና ተቋማት ይህን አገራዊ ስጋት ለመከላከል በጋራ እንዲሠሩ ጥሪ አቅርበዋል።

ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የክትትልና የቁጥጥር ሥራውን አሁንም አጠናክሮ እንደሚቀጥል በጋዜጣዊ መግለጫው ተመላክቷል።

በሺዋስ ዋለ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review