AMN- መጋቢት 19 /2018 ዓ.ም
ከንቲባ አዳነች አቤቤ የአመራር ውይይትና የስምሪት መድረክ ማካሄዳቸውን ገለጹ፡፡
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት ዛሬ ከማዕከል እስከ ወረዳ ካሉት አመራሮቻችን ጋር ሰፊ ውይይት አካሂደን ግልፅነት ፈጥረናል ብለዋል።
ከንቲባዋ አክለውም ከሃይማኖት ተቋማት ጋር ባደረግናቸው ውይይቶች ለተነሱ ጥያቄዎችና ቅሬታዎች የከተማ አስተዳደራችን ያዘጋጀው የማስፈጸሚያ ዕቅድ ላይ ተግባቦት ፈጥረናል ብለዋል።
ለዕቅዱ ተፈጻሚነትም አስፈላጊውን ስምሪት የሰጠን ሲሆን፣ አፈጻጸሙንም በቅርብ የምንከታተል ይሆናል ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡