ጣልያን ከዓለም ዋንጫ ውጪ ሆነች
AMN- መጋቢት 23/2018 ዓ.ም
ጣልያን በቦስኒያ ሄርዞጎቪና ተሸንፋ ከ2026ቱ የዓለም ዋንጫ ውጪ ሆናለች። 120 ደቂቃ የፈጀው ጨዋታ 1ለ1 ሲጠናቀቅ ሞይሴ ኪን ለጣልያን ፣ ሀሪስ ታባኮቪች ለቦስኒያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ተከላካዩ አሌሳንድሮ ባስቶኒን 41ኛው ደቂቃ ላይ በቀይ ካርድ ያጣችው ጣልያን እስከ መጨረሻው ብትፋለምም በመለያ ምት 4ለ1 ተሸንፋለች።
የአራት ጊዜ የዓለም ዋንጫ ባለቤቷ ጣልያን ለሦስተኛ ተከታታይ ጊዜ በመድረኩ የማትሳተፍ ይሆናል። ቦስኒያ በአንፃሩ ከ2014 በኋላ የመጀመሪያ የዓለም ዋንጫዋን ትሳተፋለች።
በሌላ ጨዋታ ቼክ ዴንማርክን በማሸነፍ የዓለም ዋንጫ ትኬቷን ቆርጣለች። ሁለቱ ሀገራት 120 ደቂቃውን 2ለ2 በማጠናቀቃቸው በተሰጠ የመለያ ምት ቼክ 3ለ1 አሸንፋለች።
በሸዋንግዛው ግርማ