የትንሳኤን በዓል ምክንያት በማድረግ የተከፈቱ የገበያ ባዛሮች የምርት አቅርቦትን ከማሳለጥ ባለፈ የገበያ አማራጭ እያሰፉ ነዉ

You are currently viewing የትንሳኤን በዓል ምክንያት በማድረግ የተከፈቱ የገበያ ባዛሮች የምርት አቅርቦትን ከማሳለጥ ባለፈ የገበያ አማራጭ እያሰፉ ነዉ

AMN – ሚያዝያ 02/2018 ዓ.ም

የትንሳኤን በዓል ምክንያት በማድረግ የተከፈቱ የገበያ ባዛሮች የምርት አቅርቦትን ከማሳለጥ ባለፈ የገበያ አማራጭ እያሰፉ መሆናቸዉን ሸማቾችና አምራቾች ገለጹ፡፡

በከተማዋ በሚገኙ 11ቱም ክፍለ ከተሞች ከቀናት በፊት የተከፈቱት ባዛሮች፣ ምርትን በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ በማቅረብ ረገድ ከፍተኛ ድርሻ እያበረከቱ ይገኛሉ።

ኤ ኤም ኤን ቅኝት ባደረገበት በጉለሌ ክፍለ ከተማ አካባቢ በተከፈተው ባዛር ያነጋገራቸው ሸማቾች እንደገለጹት ፣ በባዛሩ የቀረቡ ምርቶች ከሌሎች መደበኛ የግብይት ስፍራዎች ጋር ሲነፃፀሩ የዋጋ ልዩነት ያላቸውና ለኑሮ ውድነቱ እፎይታ የሰጡ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ሸማቾቹ እንደገለፁት በአካባቢያችን ከምንገዛው ሱቆች ባነሰ ዋጋ ባዛሮቹ በተመጣጣኝ ዋጋ እየገዛን ነው ብለዋል።

በባዛሮቹ ምርታቸውን በቀጥታ ለሸማቹ እያቀረቡ ያሉ አምራቾች በበኩላቸው፣ ባዛሮቹ ደላላ የሌለበት የገበያ ትስስር በመፍጠር የተሻለ ገቢ እንዲያገኙ እንደረዷቸው ገልጸዋል።

በበዓላት ወቅት የሚከፈቱ ባዛሮች ከቅዳሜ እና እሁድ ባሻገር ተጨማሪ የስራ ቀናት በመፈጠሩ ተጠቃሚ መሆናቸውን ነጋዴዎች ተናግረዋል።

ባዛሮቹ እስከ በዓሉ ዋዜማ ድረስ ክፍት ሆነው የሚቆዩ በመሆኑ ህብረተሰቡ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ መሸመት የሚችሉበት እድል መኖሩን ኤ ኤም ኤን በቅኝቱ ተመልክቷል።

በመሀመድኑር ዓሊ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review