AMN- ሚያዝያ 02/ 2018 ዓ.ም
የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ በቂ ምርቶች በስፋት እየቀረቡ መሆናቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ገለጸ፡፡
ቢሮው የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ በተከፈቱ ባዛሮች ላይ ለበዓል ፍጆታ የሚውሉ እንደ ዶሮ፤ በግ፤ ፍየል እና በሬ እንዲሁም የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርቶች ለህብረተሰቡ እየቀረቡ መሆናቸውን ገልጿል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የንግድ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ የተመራ የአመራሮች የንግድ ግብረ-ኃይል በኮልፌ፣ በአዲስ ከተማ እና በየካ ክፍለ ከተሞች በሚገኙ ባዛሮች ላይ የመስክ ምልከታና ጉብኝት አካሂዷል፡፡

ግብረ-ኃይሉ በምልከታው ወቅት እንደገለጸው በባዛሮቹ ላይ በቂ የቁም እንሰሳት እና ለበዓሉ ፍጆታ የሚውሉ ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ እየቀረቡ መሆናቸውን አረጋግጧል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ፣ ይህ አበረታች ተግባር ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ማሳሰባቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ገልጿል፡፡