በአዲስ አበባ የተከናወኑ የልማት ስራዎች ዓለምአቀፍ ተወዳዳሪነትን ያሳደጉ እና እውቅና የተቸራቸው አኩሪ ተግባራት ናቸው – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

You are currently viewing በአዲስ አበባ የተከናወኑ የልማት ስራዎች ዓለምአቀፍ ተወዳዳሪነትን ያሳደጉ እና እውቅና የተቸራቸው አኩሪ ተግባራት ናቸው – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

AMN-ሚያዝያ 23/2018 ዓ.ም

በአዲስ አበባ የተከናወኑ የልማት ስራዎች ዓለምአቀፍ ተወዳዳሪነትን ያሳደጉ እና እውቅና የተቸራቸው አኩሪ ተግባራት መሆናቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

ከንቲባ አዳነች በማህበራዊ የትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት ዛሬ በመስቀል አደባባይ “የእርጅና ገፅታን የገፈፈ፣ የውበት ፀዳል ያላበሰ ለውጥ!” በሚል ርዕስ የአምስት አመታት የልማት እና ሰው ተኮር ስራዎችን ለማሳየት የተዘጋጀ የፎቶግራፍ ኤግዚቢሽን ከፍተናል ብለዋል።

እንደሚታወቀው አዲስ አበባ ላለፉት አምስት ዓመታት ስሟን የምትመጥን መዲና እንድትሆን ከማድረግ አንፃር ከፍተኛ ስራ መሠራቱና ብዙሃኑን ተጠቃሚ ማድረግ ያስቻሉ አንፀባራቂ ውጤቶች መመዝገባቸው፣ ከአገራችን አልፎ በተለያዩ ዓለም አቀፍ መድረኮች እውቅና የተሰጠበት አኩሪ ተግባር መሆኑ የሚታወቅ ነው ብለዋ ከንቲባ አዳነች።

ከንቲባዋ አክለውም ፎቶዎቹ የመፈፀም ብቃታችንን የሚያረጋግጡ፤ በታማኝነት ማገልገልን፣ የልማት አርበኝነትንና ተነሳሽነትን የሚመሰክሩ ከመሆንም ባለፈ፣ የእድገት ራዕይ፤ የአላማ-ፅናት፤ የማያቋርጥ ትጋት የተተገበረበት በህዝብና መንግስት ጠንካራ ጥምረት እውን የሆነ የጋራ አሻራ ነው ብለዋል።

በዚህ አውደ-ርዕይ እየተዘዋወራችሁ ፎቶዎችን ስትመለከቱ ለህዝባችን የገባነውን ቃል ጠብቀን ማከናወን የቻልነውን ብቻ ሳይሆን፣ ቀሪ ስራዎችን በቀጣይ ለመስራት የሚያስችለን ምቹ ሁኔታ መፈጠሩንም በማስተዋል የበለጠ ውጤት ለማስመዝገብ በመዘጋጀት ይሁን ሲሉም አሳስበዋል።

በመጨረሻም ይህንን አውደ-ርዕይ ያዘጋጃችሁ አካላትን በሙሉ ከልብ እያመሠገንኩ ከዛሬ ጀምሮ ለ5 ቀናት ክፍት በመሆኑ እንድትጎበኙት ልጋብዛችሁ እወዳለሁ ብለዋል ከንቲባ አዳነች አቤቤ።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review