ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ዕጩ ሆነው በቀረቡበት የምርጫ ክልል ብልጽግና ፓርቲ እጩዎችን አስተዋውቋል

You are currently viewing ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ዕጩ ሆነው በቀረቡበት የምርጫ ክልል ብልጽግና ፓርቲ እጩዎችን አስተዋውቋል

AMN ሚያዝያ 28/2018 ዓ.ም

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በቀረቡበት የምርጫ ክልል ብልጽግና ፓርቲ እጩዎችን በማስተዋወቅ ቅስቀሳ አድርጓል።

በመረሃ ግብሩ ላይ በኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ የፖለቲካ ዘርፍና አቅም ግንባታ ኃላፊ ነመራ ቡሊን ጨምሮ የዞኑ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

በኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ የፖለቲካ ዘርፍና አቅም ግንባታ ኃላፊ ነመራ ቡሊ ባስተላለፉት መልዕክት ብልጽግና ፓርቲ የኢትዮጵያን ከፍታ በተግባር እያሳየ ያለ መሆኑን ጠቅሰዉ ብልጽግና ፓርቲን መምረጥ የኢትዮጵያን ልዕልና ማረጋገጥ መሆኑን ገለጸዋል።

የጅማ ዞን አስተዳዳሪ ቲጃኒ ናስር ለተሳታፊዎች ባስተላለፉት መልዕክት ብልጽግና ፓርቲ ትልልቅ ፕሮጀክቶችን በመገንባት የህዝቡን ኑሮ እያሻሻለ ያለ ፓርቲ መሆኑን የጎማ ወረዳ ህዝብ በተጨባጭ እያየ መሆኑን ጠቁመዋል።

የጎማ ሁለት ምርጫ ክልል መራጮች የኢትዮጵያ ብልጽግና መሐንዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) የመምረጥ እድል ስላገኛችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ብልጽግና ፓርቲን በመወከል ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እጩ ተወዳዳሪ በመሆን የቀረቡ ሲሆን አቶ ፉዓድ ራያ አባጊሳ፣ ወ/ሮ ኢፍቱ መሃመድ አብዱና አቶ ነዚፍ መሃመድ አሚን ሼኢሳ ለክልል ምክር ቤት እጩ በመሆን ቀርበዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review