በመዲናዋ የህግ የበላይነትን ለማስፈን በተሰራው ስራ የወንጀል ምጣኔ መቀነሱ ተገለጸ

You are currently viewing በመዲናዋ የህግ የበላይነትን ለማስፈን በተሰራው ስራ የወንጀል ምጣኔ መቀነሱ ተገለጸ

ANM- ሚያዝያ 29/2018 ዓ.ም

በአዲስ አበባ የህግ የበላይነትን ለማስፈን በተሰራው ስራ የወንጀል ምጣኔን 47 በመቶ መቀነስ መቻሉን የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊና የህግ ማስከበርና መልካም አስተዳደር ክላስተር ሰብሳቢ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ ገለጹ።

የአዲስ አበባ ከተማ የህግ ማስከበበርና መልካም አስተዳደር ክላስተር የ9 ወራት የዕቅድ አፈፃፀሙን እየገመገመ ይገኛል። የቢሮ ኃላፊዋ እና የክላስተሩ ሰብሳቢ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ በተያዘው በጀት ዓመት ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ ውጤታማ ስራ መሰራቱን አብራርተው ፣ ነዋሪውን የሰላም ባለቤት በማድረግ በከተማዋ ዘላቂ ሰላምን ማስፈን መቻሉን አንስተዋል።

በከተማዋ የተከናወኑ የአደባባይ ሁነቶችና ሀገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ ሁነቶች ፍፁም ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ማድረግ ተችሏል።

ከንግድ ጋር በተያያዘ ከንግድ ቢሮ ጋር በመተባበር ህገወጥ ነጋዴዎችን ቁጥጥር የማድረግና ወደ ህጋዊ መንገድ ማስገባት ፣ በከተማዋ በተለያዩ ምርቶች ላይ ኣላስፈላጊ የዋጋ ጭማሬ እንዳይኖርና ሰው ሰራሽ የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይፈጠር ባለፉት ዘጠኝ ወራት በቅንጅት ስለመሰራቱም አንስተዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በህግ ማስከበርና መልካም አስተዳደር ክላስተር ከተለያዩ ተቋማት ጋር በቅንጅት በተሰራው ስራ ውጤት የተመዘገበበት እንደነበር በመድረኩ ተመላክቷል።

የግምገማ መድረኩ ተሳታፊዎች የነበሩ ጥንካሬዎችን ማስቀጠል የታዩ ጉድለቶችን በቀሪ ወራት በላቀ መፈጸም እንደሚባ አመላክተዋል።

በመሀመድኑር ዓሊ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review