በዓለም አቀፍ ተጽእኖ ምክንያት ሊከሰቱ የሚችሉ የገበያ መዛባቶችንና የኑሮ ጫናን ለመቀነስ እየተወሰዱ ያሉት የመፍትሔ እርምጃዎች ተጠናክረዉ ይቀጥላሉ -ከንቲባ አዳነች አቤቤ

You are currently viewing በዓለም አቀፍ ተጽእኖ ምክንያት ሊከሰቱ የሚችሉ የገበያ መዛባቶችንና የኑሮ ጫናን ለመቀነስ እየተወሰዱ ያሉት የመፍትሔ እርምጃዎች ተጠናክረዉ ይቀጥላሉ -ከንቲባ አዳነች አቤቤ

AMN- ሚያዝያ 30/2018 ዓ.ም

የኑሮ ውድነት ለማቃለል የምርት አቅርቦትን መጨመርና የንግድ ሰንሰለቱን የሚያሳጥሩ የተለያዩ ተግባራት መከናወናቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባኤውን ያካሄደ ሲሆን፤ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የምክር ቤቱ አባላት ላነሷቸው አስተያየቶችና ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በማብራሪያቸውም የኑሮ ውድነት ላይ ከተማ አስተዳደሩ ትኩረት አድርጎ እየሰራ እንደሚገኝ አንስተዋል፡፡

የኑሮ ውድነት በኢትዮጵያ ብቻ የተከሰተ አለመሆኑን መረዳት ያስፈልጋት ያሉት ከንቲባዋ፤ የኑሮ ውድነትን ያስከተሉ ጉዳዮች በኢትዮጵያ ሁኔታ ብቻ እንደማይወሰኑ ምክር ቤቱ እንደሚረዳው እምነት እንዳላቸውም ተናግረዋል፡፡

በዓለም አቀፍ ተጽእኖ ምክንያት እና በሃገራችን ሁኔታዎች የሚከሰቱ የገበያ መዛባቶች የሚደርሱ የኑሮ ውድነት ችግሮች እንዳይባባሱ መንግስት ትኩረት አድርጎ እየሰራ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

የኑሮ ውድነት ችግሮችን ለመፍታትም የሃገር ውስጥ የምርት አቅርቦትን መጨመር፣ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን መጠን በመቀነስ ተኪ ምርቶችን ማምረት አስፈላጊ ነው ያሉት ከንቲባዋ ፣ የኑሮ ውድነት ላይ ያለውን ጫና ለመቀነስ ከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ ትኩረት የሰጠው ጉዳይ መሆኑንም አንስተዋል፡፡

የክትትልና የቁጥጥር ሥራች ላይ አበረታች ስራዎች እንደተሰሩም በመግለጽ በአዲስ አበባ ትልልቅ የመግቢያ በሮች የገበያ ማእከላት ተገንብተው ስራ ጀምረዋል ብለዋል፡፡

ከየትኛውም አካባቢ ምርት በቀጥታ ገብቶ አዲስ አበባ ላይ ተደራሽ እንዲሆን እና ደላላ እንዳይገባ የቁጥጥር ስራ መሰራቱን ጠቅሰው ህገወጥ ተግባራት ላይ የተሰማሩ 18 ሺህ 400 ነጋዴዎች መቀጣታቸውን አስታውሰዋል፡፡

የንግድ ኮርፖሬሽን በማቋቋምና ድጋፍ በማድረግ ምርቶች ለህዝቡ እንዲቀርቡ በመደረጉ በተገነቡ የገበያ ማእከላትም ህብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ የሚፈልገውን ሁሉ ማግኘት እንዲችል ተደርጓል ነው ያሉት፡፡

በከተማዋ ያሉ ገበያ ማእከላትንም በማስፋት ዜጎች ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሰው ለመግዛት የሚያወጡትን የትራንስፖርት ወጪ መቀነስ እንደተቻለ ተነስቷል፡፡

በየአካባቢው አምራቾች እና ጅምላ አከፋፋዮች በተለይም ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች የኢንዱስትሪ ምርቶችን እና የገበያ አማራጮችን እንዲያገኙ እየተሰራ ስለመሆኑም ተገልጿዋል፡፡

የሻምበል ምሕረት

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review