‎መረጃ የዚህ ዘመን ስትራቴጂካዊ ሀብት እና ጠንካራ ሀገረ መንግሥት የሚገነባበት ቁልፍ የሉዓላዊነት ምሰሶ ነዉ – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

You are currently viewing ‎መረጃ የዚህ ዘመን ስትራቴጂካዊ ሀብት እና ጠንካራ ሀገረ መንግሥት የሚገነባበት ቁልፍ የሉዓላዊነት ምሰሶ ነዉ – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

AMN- ግንቦት 10/ 2018 ዓ.ም

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ የትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት ”የመረጃ ሉዓላዊነት ለፖሊሲ ነጻነት” በተሰኘውና ኢትዮጵያ በመረጃና በስታቲስቲክስ የሉዓላዊነት ጉዞ ያስመዘገበችውን ትልቅ ድል በተበሰረበት ሀገራዊ ጉባኤና ኤግዚቢሽን ላይ ተገኝቼ የተመለከትኩት የዘርፉ እመርታ እጅግ አስደሳች ሆኖ አግኝቼዋለሁ ብለዋል።

‎መረጃ የዚህ ዘመን ስትራቴጂካዊ ሀብት እና ጠንካራ ሀገረ መንግሥት የሚገነባበት ቁልፍ የሉዓላዊነት ምሰሶ መሆኑን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ የተዋሰ አሊያም በውጭ አካላት ላይ ጥገኛ የሆነ መረጃ ሀገራዊ መሻታችንን ማሳካት ስለማያስችል፤ የፖሊሲ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የራስን መረጃ በራስ አቅም መሰብሰብ እና መተንተን ወሳኝ ግብዓት ነው ብለዋል።

‎ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም ከሁሉም በላይ፤ የመረጃ አሰባሰብና ትንተና ሥራ በሀገር ልጆች እውቀትና ክህሎት ሲከወን ማየት ታላቅ ሀገራዊ ኩራት ነው። ከዚህ በተጨማሪ የመረጃ ትኩረታችን በቁጥር በሚገለጹ ውጤቶች ላይ ብቻ ሳይሆን ሰው ተኮር በሆኑና በዜጎች ሕይወት በሚታዩ ተጨባጭ ለውጦችም ላይ መሆን አለበት ብለዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review