የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር የተፈጥሮን ጉዳት እያከመ ለመሆኑ የሀሮማያ ሐይቅ ህያው ማሳያ ነው- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ

You are currently viewing የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር የተፈጥሮን ጉዳት እያከመ ለመሆኑ የሀሮማያ ሐይቅ ህያው ማሳያ ነው- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ

AMN- ግንቦት 10/ 2018 ዓ.ም

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ በማህበራዊ የትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር የተፈጥሮን ጉዳት እያከመ ለመሆኑ የሀሮማያ ሐይቅ ህያው ማሳያ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የሀሮማያ ሐይቅ ዳግም መወለድ አረንጓዴ አሻራ ከሰጠን ፍሬዎች አንዱ ነው። በ1996 ዓ.ም ሙሉ በሙሉ ጠፍቶ የነበረው የሀሮማያ ሐይቅ፣ በአረንጓዴ አሻራ እና በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ጥረት ዛሬ ወደ ቀደመ ውበትና ሥሪቱ ተመልሷል ብለዋል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ።

ይህም አረንጓዴ አሻራን ለኢትዮጵያ የውሃ አካላትና ለተፋሰስ ልማት ቁልፍ ኢኒሼቲቭነቱን በተግባር ያረጋገጠ ነው።

አቶ ተመስገን አክለውም ይህ ስኬት በመደመር እሳቤ ልማትን ማረጋገጥ ብቻ ሳይሆን፣ የተፈጥሮን ጫና መቋቋም እና መግራት እንደሚቻል ማረጋገጫ ነው ብለዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአካባቢው ስንደርስ ለተደረገልን አቀባበል ምስጋና አቀርባለሁ ሲሉም ለተደረገላቸው አቀባበል ያላቸውን ምስጋና አቅርበዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review