ከዓለም የከተሞች ፎረም ተሳትፎ ጐን ለጐን የአዘርባጃንን የአሳን ቀላል የአንድ ማዕከል ዲጂታል አገልግሎትን ጉብኝተናል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

You are currently viewing ከዓለም የከተሞች ፎረም ተሳትፎ ጐን ለጐን የአዘርባጃንን የአሳን ቀላል የአንድ ማዕከል ዲጂታል አገልግሎትን ጉብኝተናል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

AMN ግንቦት 11/2018 ዓ.ም

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት ከዓለም የከተሞች ፎረም ተሳትፎ ጐን ለጐን የአዘርባጃንን የአሳን ቀላል የአንድ ማዕከል ዲጂታል አገልግሎትን (ASAN-Azerbaijan Service and Assessment Network) ጉብኝተናል ብለዋል፡፡

እኛም እስከአሁን በመሶብ ዲጂታል የአንድ ማዕከል አገልግሎት ያመጣነው ከፍተኛ ለውጥ ቢሆንም፣ አሁንም ልምድ ሊሆኑን በሚችሉ ጉዳዮችም ላይ ውይይት አድርገናል።

ከ14 ዓመታት በፊት የተጀመረው እና በቀን 40ሺህ አፕሊኬሽን ላይ አገልግሎት የሚያሳልጠው አሳን፣ በአውቶቡሶች የሚሰጥ የገጠር አካባቢዎች ተንቀሳቃሽ የአገልግሎት ማዕከል በተደራጀ፣ ፈጣን ቀላል አገልግሎት ይሰጣሉ ብለዋል፡፡

በሀገራችን ኢትዮጵያም ከ41 በላይ ማዕከላት ገንብተን ስራ የጀመርን ሲሆን፣ ከዚሁ ውስጥ በአዲስ አበባ 6 ማዕከላት እና 1 ተንቀሳቃሽ አውቶቡስ የዲጂታል የአንድ ማዕከል አገልግሎት የሚሰጡ ማዕከላት እንዳሉን ይታወቃል።

የአሳን ሰራተኞች አገልግሎት ሲሰጡ ፈገግታ እና ትህትና አንዱ የአገልግሎት መለኪያ እንደሆነ፣ የመከታተያ ካሜራዎች የተገጠሙ መሆኑን እና በጥሩ ሁኔታ የሚያገለግል ሰራተኛ ተመዝኖ እና የተገልጋዩ የዕርካታ መጠን ከፍተኛ ከሆነ ከደሞዝ በተጨማሪ ቦነስ እንደሚከፈለው ተመልክተናል። በዛው ልክ በመስፈርቱ መሰረት ያላገለገለ ወዲያው ይባረራል። ለነገ ተስፋ አድገው ህዝባቸውን በከፍተኛ ትጋትና አክብሮት የሚያገለግሉ በርካታ በጎ ፍቃደኛ ወጣቶችንም ተመልክተናል።

የእኛም ቢሮክራሲ በተጀመረው አግባብ ሙሉ በሙሉ እንደሚለወጥ እናምናለን ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review