AMN ግንቦት 11/2018 ዓ.ም
በአዲስ አበባ እና በባኩ መካከል የእህትማማች ከተሞች ስምምነት ስምምነት መፈራረማቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።
ከአዘርባጃን ዋና ከተማ ባኩ ጋር የተፈራረምነው ስምምነት፤ በከተማ ልማት፣ በአገልግሎት ዲጂታላይዜሽን፣ በቤት ልማት፣ በቱሪዝም (ስፖርት ቱሪዝምን ጨምሮ) እና በሁለቱ ህዝቦች መካከል የባህልና የታሪክ ልውውጥን የሚያጠናክር የእህትማማች ከተማ ስምምነት (Sister Cities agreement) ነው ሲሉ ከንቲባዋ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል።