AMN-ግንቦት 11/2018 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ገበያ ማረጋጋት ላይ ትኩረት አድርጎ ከልደታ ክፍለ ከተማ የንግዱ ማህበረሰብ ጋር ውይይት አካሄዷል።
በውይይት መድረኩ ላይ የተገኙት የቢሮው ኃላፊዋ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር የመወያየት አላማው ባለፉት 5 ዓመታት የተተገበሩ ስራዎችን በጋራ ለመገምገምና ለቀጣይ 5 ዓመታት እቅድ ግብአት ለማሰባሰብ ነው ብለዋል።
የንግዱ ማህበረሰብ ቢሮ ሳይሄድ ባለበት ሆኖ በኢንተርኔት በይነ መረብ አገልግሎት እንዲያገኝ በተሰራው ስራ ውጤት ተመዝግቧል ብለዋል።
በአቅርቦት በኩልም ቀደም ሲል በጥቂት ከፍተኛ ነጋዴዎች በብቸኝነት ተይዞ የነበረውን ምርቶችን በሞኖፖል የመያዝ አሰራር በማሻሻል ዝቅተኛ ነጋዴው ጭምር ተሳትፎ ምርቶችን በስፋት ወደ ከተማዋ እንዲገቡ የተደረገው ባለፉት የለውጥ አመታት እንደሆነም ነው ያነሱት።
ባለፉት 5 ዓመታት ከየትኛውም ጊዜ በላይ የነጋዴው ማህበረሰብ ጥያቄ የተመለሰባቸው አመታት እንደነበሩም የንግድ ቢሮ ኃላፊዋ ወ/ሮ ሃቢባ ሲራጅ አስታውቀዋል።

የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ በበኩላቸው የንግዱ ማህበረሰብ ትርፍን ታሳቢ ካደረገው ስራው በዘለለ ከተማ አስተዳደሩ በሚያቀርብለት የማህበራዊ ልማት ተሳትፎዎች ሁሉ ጉልህ አስተዋጽኦ ሲያበረክት መቆየቱን ተናግረዋል።
በልደታ ክፍለ ከተማ በተገነቡ 32 የልማት ፕሮጀክቶች የንግዱ ማህበረሰብ ከፍተኛ ድጋፍ በማድረግ ማገዙንም ተናግረዋል።
በቀጣይም በንግዱ ዘርፍ ላይ ያተኮሩ የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ላይ የላቀ ትኩረት ሰጥቶ ከነጋዴው ህብረተሰብ ጋር በበለጠ ተቀራርቦ ለመስራት የውይይት መድረኩ መዘጋጀቱንም ጠቅሰዋል።
በውይይት መድረኩ ላይ ከሁሉም የልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳዎች የተውጣጡ የንግዱ ማህበረሰብ ተወካዮች እየተሳተፉበት ነው።
በምትኩ ተሾ