AMN- ግንቦት 21/2018 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የሀገራዊ ምክክር ረቂቅ አጀንዳዎችን ለምሁራን እና ተባባሪ ተቋማት አቅርቦ ምክረ ሀሳብ ያሰባሰበበትን መድረክ አካሂዷል።

ግንቦት 21 ቀን 2018 ዓ.ም ባካሄደው መድረክ የግል፣ የመንግስት እንዲሁም የሃይማኖት ትምህርት ተቋማት እና የተለያዩ ምርምር ማዕከላት ምሁራን ተሳትፈዋል።
ኮሚሽኑ ባለፉት ቀናት መሰል መድረኮችን ከመንግስት፣ ከሃይማኖትና ሲቪክ ተቋማት እንዲሁም ከአጋር አካላት ጋር ማካሄዱ ይታወሳል።

ይህ የሀገራዊ ጉባኤ ረቂቅ አጀንዳዎች ቀርበው ግብዓት የሚሰበሰብበት መድረክ በቀጣይ ቀናትም የፓለቲካ ፓርቲዎችን ጨምሮ ከተለያዩ ተቋማትና ባለ ድርሻ አካላት ጋር ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።