19ኛው ግማሽ ማራቶን ለሐገር ዓቀፍ ውድድሮች መነቃቃት አስተዋጽኦ አለው – አትሌት ስለሺ ስህን

You are currently viewing 19ኛው ግማሽ ማራቶን ለሐገር ዓቀፍ ውድድሮች መነቃቃት አስተዋጽኦ አለው – አትሌት ስለሺ ስህን

AMN ግንቦት 30/2018

በአዲስ አበባ በታላቅ ድምቀት የተካሄደው 19ኛው የኢትዮጵያ ግማሽ ማራቶን የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ከፍተኛ ፉክክር የተደረገበት መሆኑን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አትሌት ስለሺ ስህን ገለጹ።

ፕሬዝዳንቱ በተለይ ለኤ ኤም ኤን በሰጡት ማብራሪያ የዘንድሮው ውድድር ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የተሳታፊዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ የጨመረበትና ለሀገር ዓቀፍ ውድድሮች መነቃቃት አስተዋጽ ያለው ነው ብለዋል፡፡

ውድድሩ አትሌቶች በጉጉት የሚጠብቁትና ክለቦች እንዲሁም ክልሎች ከፍተኛ ፉክክር የሚያደርጉበት መሆኑን ነው አትሌት ስለሺ የገለጹት፡፡

ተተኪ አትሌቶች ከነባርና ልምድ ካላቸው አትሌቶች ጋር አብረው በመወዳደር ራሳቸውን እንዲመዝኑ እና ብቃታቸውን እንዲያሳድጉ ዕድል የሚፈጥ ነው ብለዋል።

ውድድሩ ዓመታዊ እንደመሆኑ መጠን ከሁሉም የሀገሪቱ ክልሎች የመጡ አትሌቶች የተሳተፉበት መሆኑንም ገልጸዋል።

ይህ አገር አቀፍ ውድድር በዴንማርክ ኮፐንሀገን ለሚካሄደው ማራቶን ኢትዮጵያን ወክለው የሚሳተፉ አትሌቶች የሚመረጡበት መሆኑን ፕሬዝዳንቱ አስገንዝበዋል።

በዘንድሮው ዓመት በአጠቃላይ የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድሮችን የማዘጋጀት እንቅስቃሴ ከሌላው ጊዜ በበለጠ መልኩ ከፍተኛ መነቃቃት የታየበት እና ደረጃው ከፍ ያለ እንደነበር አትሌት ስለሺ ስህን በጥንካሬ አንስተዋል።

በፍሬሕይወት ብርሃኑ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review