አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክና ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ

You are currently viewing አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክና ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ

‎AMN – ሰኔ 11/2018 ዓ.ም

‎አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክና ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።

‎‌‎ስምምነቱን የፈረሙት የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሰለሞን ዲባባ እና የኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃለፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ዋና ስራ አስፈጻሚ ኮማንደር ጥላሁን ፀጋዬ ናቸው፡፡

የኤኤምኤን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሰለሞን ዲባባ በወቅቱ እንደተናገሩት፤ ተቋሙ ከከተማዋ ልማትና እድገት ጋር አብሮ በማደግ ላይ ያለ ተወዳዳሪ ሚዲያ መሆኑንም ገልፀዋል።

ተቋሙ በኤኤምኤን ቴሌቭዥን ፣ በኤኤምኤን ፕላስ፤ በሬዲዮ፣ በሕትመት እንዲሁም በዲጂታል ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን በፍጥነት እና በጥራት ተደራሽ በማድረግ የብዙኃን አንደበት ሆኖ እያገለገለ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

‎ተቋሙ በአሁኑ ወቅት በሰባት ቋንቋዎች መረጃዎችን ለአድማጭ ተመልካች እያቀረበ መሆኑን ገልጸው፤ በተጨማሪ ሦስት ቋንቋዎች መረጃዎችን ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

‎አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ የሜትሮፖሊታን ሚዲያ እንደመሆኑ የከተማዋን ዘመናዊነት፣ የጽዳትና የውበት ስራዎችን እንዲሁም የአሰራር ደረጃዎችን የጠበቁ እንዲሆኑ ለማድረግ ከሚሰሩ ተቋማት ጋር ያለውን አጋርነት አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡

የኮሜርሻል ኖሚኒስ ዋና ስራ አስፈጻሚ ኮማንደር ጥላሁን ፀጋዬ በበኩላቸው ፤ የተቋማቸው ራዕይ እና ግብ ለማሳካትና ተደራሽነቱን ወደ ሰፊው ማህበረሰብ እና ደንበኞቹ ለማስፋት ከአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ጋር የስራ ስምምነት መፈራረሙን አብራርተዋል፡፡

አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ በቅርቡ ባካሄደው መጠነ-ሰፊ የሪፎርም ስራ እራሱን ይበልጥ በማጠናከር ላይ ይገኛል ያሉት ኮማንደር ጥላሁን ፤ በሁሉም የመገናኛ ብዙኃን አማራጮች በጋራ በመስራት ሁለንተናዊ እድገት ለማስመዝገብ መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።

ዋና ስራ አስፈጻሚው አክለውም፣ ሚዲያው ተቋማቸውን ወደ ማህበረሰቡ እና ወደ ደንበኞቻቸው ይዞ በመቅረብ፣ መረጃዎችን በተገቢው መንገድ በማድረስ ረገድ የሚኖረው ሚና የጎላ ስለመሆኑ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

በሄለን ጀንበሬ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review