AMN – ሰኔ 16/2018 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ለ250 አካል ጉዳተኞች የሚያገለግሉ ግብዓቶችን አስረከበ።
ቢሮው በበጀት ዓመቱ የዛሬውን ጨምሮ 2 ሺህ 570 የአካል ድጋፎችን ለተጠቃሚዎች ያበረከተ ስለመሆኑ ያነሱት የቢሮው ኃላፊ ወይዘሮ ቆንጅት ደበላ ፣ አካል ጉዳተኞች የማህበረሰቡ አካል በመሆናቸው ድጋፉ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

በዛሬው ዕለትም ለህፃናት 150 እና ለአዋቂዎች 100 የአካል ድጋፎች ለተጠቃሚዎች መሰጠቱን ኃላፊዋ አንስተዋል ።
ድጋፉ በተለይ ለህፃናት ትኩረት የሰጠ መሆኑንና ህፃናት በአካል ድጋፉ እጦት ምክንያት ከትምህርት ገበታቸው እንዳይሰናከሉ ድጋፉ መደረጉ ተገልጻል።
የአካል ድጋፍ ባለማግኘታቸው በርካታ ተግዳሮቶችን ያስተናገዱ ስለመሆኑ ያነሱት የአካል ድጋፍ የተበረከተላቸው ዜጎች ስጦታው ችግራቸውን የሚያቀልላቸው ስለመሆኑም ተናገረዋል።
ጽዮን ማሞ