AMN – ሰኔ 18/2018 ዓ.ም
የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር በኢትዮጵያ የማር ምርት ላይ ተጨባጭ ውጤት እያስመዘገበ ይገኛል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ለአየር ንብረት ጥበቃ መሠረታዊ አስተዋፅዖ እያበረከተ ነው ብለዋል።
ከዚህ ባለፈም በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ የማር ምርት ላይ ተጨባጭ ውጤቶችን እያስመዘገበ ይገኛል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ተፈጥሮንና አካባቢያችንን በመጠበቃችን፣ ደኖች እየተስፋፉ በመምጣታቸው፣ የንብ ዝርያዎችን የሚያግዙና የማር ምርትን የሚያሳድጉ ምቹ ከባቢዎች ምክንያት የምግብ ምንጮች ሊፈጠሩ ችለዋልም ብለዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) “ተስፋን እንትከል!” ሲሉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡