AMN ሰኔ 19/2018
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልዕክት ብልጽግና ፖርቲ ለ7ኛዉ ጠቅላላ ምርጫ ያቀዳቸዉ ግቦች በመሳካታቸዉ ምስጋና አቅርበዋል።
የከተማዋ ባለሀብቶች የብልፅግና ፖርቲ ሃገሪቱን ለመገንባትና ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ተጠቃሚ የሚያደርግ ፓሊሲና ስትራቴጂ ነድፎ እየተጋ መሆኑ ገብቷቸዉ ግልፅ አቋም ይዘዉ የሁሌም አጋርና ግንባር ቀደም ሆነዉ በሁሉም መልኩ በንቃት በመሣተፍ ላደረጉት ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።
ከንቲባዋ በመልዕክታቸዉ የኢትዮጵያ ምርጫ የአንድ ፓርቲ አብላጫ ድምፅ ከማግኘት በላይ ከፍ ያለ ሀገርን የማፅናት ተግባር መሆኑንም ገልጸዋል።

ህዝቡ በምርጫዉ ለዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ያለዉን ጽናትና፥ የተጀመረውን የሀገር ልማት ለማስቀጠል ያለውን ፍላጎት ማሳየቱን የገለጹት ከንቲባዋ ሰላምን ዘላቂ የማድረግ ጉዞ እንዲሳካ ለፓርቲዉ ዳግም ታላቅ ኃላፊነትና አደራ መስጠቱንም ተናግረዋል።
በተሰጠን ሃላፊነት በእውነት፥ በትጋት እና በቅንነት በማገልገል ህዝባችንን እንክሳለን ሲሉም አጽንኦት ሰጥተዋል።
ፓርቲያችን በግሉ ሴክተር ጠንካራ አጋርነት ብልፅግናችን ይሳካል ብሎ ያምናል ያሉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለዚህም የግሉ ሴክተር ለሃገር ግንባታ በምታደርጉት ጥረት ሁሌም ድጋፋችን አይለያችሁምና በትብብር መስራታችንን አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።