ኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ አሰልጣኝ ገብረ መድህን ሃይሌ መሾሙን ይፋ አደረገ

AMN-ሐምሌ 9/2018 ዓ.ም

ኢትዮጵያ ቡና የቀድሞ አሰልጣኙ ገብረመድህን ሃይሌ መሾሙን ዛሬ ይፋ አድርጓል።

ለቀጣይ ሁለት ዓመታት ለመቆየት የተስማማው አሰልጣኙ ከ16 ዓመታት በኃላ ወደ ቡና የተመለስኩት ለክለቡ ታሪክ ለመስራት ነው ብሏል::

ከ20 ቀናት በኋላ በይፋ ስራ የሚጀምርው እሰልጣኙ ጠንካራ ቡድን በመገንባት በደጋፊው በጥብቅ የሚፈለገውን የሊጉን ዋንጫ ለማሳካት እንዳሰበ ገልጿል::

የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ከፍተኛ አመራሮች በቡና ስም ጠንካራ የሆነ ተቋም እንዲኖር እንጂ ውጤታማ ያልሆነ ጉዞ ስለማይመጥን አስፈልጊውን ድጋፍ እናደርጋለን ብለዋል::

በዮናስ ሞላ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review